አንድ የደሃ ቤተሰብ ልጅ


አንድ የደሃ ቤተሰብ ልጅ እጅግ በጣም የሃብታም የሰፈሩን ልጅ ያፈቅራል፣እንዲሁ

በ ሰፈር ጓደኝነት አብረው ጥሩ ጊዜ ካሳለፉ በኋላ በውስጡ የሚቀጣጠለውን

ፍቅሩን ለመግለጽ ቀን እና ሰአት ጠብቆ የፍቅር ጥያቄ ያቀርብላታል: እሷም

ይህን መለሰች "ምን አልክ?! ፍቅረኞች እንሁን?!፣ካንተጋር ጊዜ ማሳለፌን በሌላ

ተረድተኸው ከሆነ ተሳስተሃል፣በዛላይ እኔና አንተ ይምንመጣጠን ሰዎች

አይደለንም አንተ መናጢ ደሃ ነህ በወር የምታገኘውን ገንዘብ እኔ በአንድ ሰአት

ከጓደኞቼ ጋር ማጠፋት ናት በምን ልታኖረኝ ነው? ይሄን ሃሳብህን ተውና ሌላ

ምትመጥንህን ሴት ፈልግ እኔ እንደሆነ መቼም ላፈቅርህ አልችልም" ይሄን

ብላውም ልጁ በፍጹም ሊጠላት አልቻለም፣ ስለገፋችው ብቻ ከሷ ራቀ ልቡ ግን

ሁሌም እሷ ጋር ነበር ከ10 አመታት ቡሀላ አንድ ቀን እንዳጋጣሚ ሱፐር ማርኬት

ውስጥ ከልጅቷ ጋር ይገናኛሉ: "አነተ እንዴት ነህ? አለህ እንዴ? አሁንማ እዛ ጋር

መኪና ውስጥ እቃ የሚያስገባውን ምርጥ ሰው አገባሁኝ ስማርት ነው በዛ ላይ

በወር ስንት እንሚያገኝ ታውቃለህ 15,000 ብር ይሄን ሚበልጥ ደሞዝ ካለህ

አሁንም እድሉ አለህ ሃሃሃሃ..." ልጁ ከአስር አመት በኋም ይሄን ቃል

ከሚያፈቅራት ልጅ በድጋሚ መስማቱ አስለቀሰው፣ እንባዎቹን እየጠረገ ሳለ

የልጅቷ ባል መጣና:- "ጌታዬ ባለቤቴን ተዋወቃት" አለና ወደ ልጅቷ ዞሮ:

"ይገርምሻል ይሄንን ሱፐር ማርኬት እና ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠር ካፒታል

ያላቸው ድርጅቶች ባለቤት የሆነው አለቃዬ እሱ ነው: እስካሁን አላገባም: አንድ

በጣም የሚያፈቅራት ልጅ ነበረች በንጹህ ፍቅር የወደዳት ልቧን ግን ማሸነፍ

አላቻለም: እንዴት ያለ መልካም ሰው መሰለሽ: መቼም እሱን ያገኘች ሴት

በሁሉም ነገር አላህ ፈጣሪ የባረካት እድለኛ ሴት መሆን አለባት።

ልጅትዋ ደርቃ ቀረች

Comments

Popular posts from this blog

Jvzoo

Money making